top of page

የእምነት አቋማችን

  1. በማይበተን አንድነት፣ በማይጨፈለቅ ሦስትነት ሕልው ሆኖ በሚኖር ሥሉስ ቅዱስ (ሥላሴነት) እርሱም በእግዚአብሔር አብ ፣ በእግዚአብሔር ወልድና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እናምናለን፡፡

  2. የሚታየውንና የማይታየውን ፣ ረቂቅና ግዙፉን ዓለም በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ ፈጥሮ በሚመግብ በሚጠብቅና በሚያስተዳደር በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡

  3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ ቅድመ ዓለም በመለኮታዊ ባሕርይ ከአብ የተወለደ (የተገኘ) ድኅረ ዓለም ያለ አባት ከድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ፣ ስለ ዓለሙ ሁሉ ኃጢአት በፈቃዱ ተላልፎ በመሰጠት በሞቱና በትንሣኤው የኃጢአት ይቅርታንና በስሙ በማመን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባትን እንደሰጠ እናምናለን፡፡

  4. ከአብና ከወልድ ጋር ለዘላለለም በነበረ ቅዱስ መንፈሱ (መንፈስ ቅዱስ) መለኮታዊ ሀልዎት ግብር (ሥራ) እና ሥጦታዎች እናምናለን፡፡

  5. መንፈስ ቅዱስ በነቢያትና በሐዋርያትም ዘመን እንደሠራ እስከ ፍጻሜ ዓለምም በቤተክርስቲያን በኩል ዛሬም እንደሚሰራ እናምናለን፡፡

  6. ስድሳ ስድስቱ ቅዱሳት መጽሐፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) እግዚአብሔር በተለየ መንገድና ራሱ ለዚሁ ሥራ በለያቸው ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ ፣ ስኅተት የሌለበት ፣ የማይሻር ባለሥልጣን የሆነ የእግዚብሔርን ፈቃድ ዓላማና ኃሳብን የያዘ የሕያው እግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን፡፡

  7. ድነት በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ሞት ብቻ በጸጋ ለሰዎች ሁሉ የተሰጠ በእምነት ብቻ የምንቀበለው የእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር መግለጫ እንደሆነ እናምናለን፡፡

  8. በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ እንደዳንን ሁሉ ፤ በጸጋው መኖር እንደሚገባንም እናምናለን፡፡

  9. በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ተመሥርታ በመንፈስ ቅዱስ መውረድ በተገለጠችው የመንግሥቱ ልጆች ኀብረት በሆነች ሐዋርያት በሰበሰቧትና በትምህርታቸው በምትኖር በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡

  10. በሙታን የሥጋ ትንሣኤ፣ በጻድቃንና በሕያዋን የመጨረሻው ፍርድ በዓለም ፍጻሜ እናምናለን፡፡

  11. የመንግሥቱ ዜጎች በክርስቶስ የተሰጣቸውን የኃጢአት ይቅርታና በእርሱም በማመን የተቀበሉትን ድነት እንዲሁም ወደ መንግሥቱ ዜጎች መጨመራቸውን በሚመሰክሩበት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም በሚፈጸም ሥርዓት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ፡፡

  12. ከአንድ አባት መወለዳችንን የአንድም ቤተሰብ አባላት መሆናችንን በሚገልጠው በጌታ የኅብረት ማዕድ የጌታንም ሞት ለማሰብ በሚያስችል ቅዱስ ቁርባን እናምናለን፡፡

 

ማስታወሻ፡- ለተጨማሪ ማብራሪያ የከሣቴ ብርሃን ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አሥተምህሮ የሚለውን መጽሐፍ ይመልከቱ፡፡

ራዕያችን

የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ የምታደርስ የታደሰች ቤተ ክርስቲያን ለማየት።

ተልዕኳችን

ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ ለማዳረስ

 

ወንጌልን የተቀበሉ ሰዎችን በእግዚአብሔር ቃል እና በተሃድሶ ተልእኮ ለማሰልጠን

በእግዚአብሔር ቃል የሰለጠኑ ሰዎችን ማደራጀት።

የተደራጁ ሰዎችን የወንጌል መልእክት ለመላክ እና ለማሰማራት

የእኛ እሴቶች

ተሐድሷዊነት

 

ምሳሌያዊነት

 

ባለ አደራነት

 

መሰጠት ​

ታማኝነት

አሳታፊነት

ከሣቴ ብርሃን ሐዋርያዊት ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ዲጂታል ሚድያ

ከሣቴ ብርሃን ሐዋርያዊት ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ዲጂታል ሚድያ

ከሣቴ ብርሃን ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ምጥን መረጃ ያግኙ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት አስተምህሮዎችን እና ትውፊቶችን በቪዲዮአችን ይመልከቱ። ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ከሆናችሁ ወይም የረዥም ጊዜ አባል የነበራችሁ፣ ይህ ቪዲዮ መንፈሳዊ ትስስራችሁን እና ግንዛቤን ለማሳደግ መነሳሳትን ይሰጣል።

ስለ እኛ

የከሳቴ ብርሃን ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተባረረች በኋላ በአዲስ አበባ በ1992 ዓ.ም. በተሃድሶ አራማጆች፣ ካህናትና ምእመናን አንድነት የተመሰረተችና ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ተሐድሶ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች እያገለገለች ያለች ቤተ ክርስቲያን ናት።

 

ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራው በቅዱስ ሲኖዶስ እና በሀገር አቀፍ መሪ ነው፤ ተጠያቂነቱ እና ኃላፊነቱ በየጊዜው በውጭ እና በውስጥ ባለስልጣናት ይገመገማል; ዋና መሥሪያ ቤቱን በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በማድረግ ነፃነትን እና ግልጽነትን እንደ የሥራ መርሆው ይከተላል።

አድራሻችን

አዲስ አበባ አጥቢያ

 

ከመገናኛ ወደ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ቀጥሎ ቤዛ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።

 

በጎግል ካርታዎች ላይ ይመልከቱ

  • Youtube
  • Whatsapp
  • Facebook
  • Telegram
  • TikTok

ከአዲስ አበባ ውጪ

 

ስለ መደበኛ ስብሰባዎቻችን እና የጸሎት ቡድኖቻችን ለማወቅ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

መልእክት ፃፉልን

ውሎች እና ሁኔታዎች

የግላዊነት ፖሊሲ

© 2025 በከሳቴ ብርሃን ኤሌክትሮኒክስ እና ዲጂታል ሚዲያ ቡድን።


በዊክስ የተጎላበተ እና ደህንነቱ የተጠበቀ

የተደራሽነት መግለጫ

bottom of page